ይህ ፕሮጀክት ጀማሪዎች የመጀመሪያ አስተዋጾ የሚያደርጉበትን መንገድ ለማቅለል እና ለመምራት ያለመ ነው። የመጀመሪያዎን አስተዋፅዖ ለማድረግ ከፈለጉ ከታች ያሉትን ደረጃዎች ይከተሉ
command line ካልተመቸህ, GUI መሳሪያዎችን በመጠቀም አጋዥ ስልጠናዎች አሉ።.
በማሽንዎ ላይ git ከሌለዎት, ይጫኑት.
በዚህ ገጽ ላይኛው ክፍል ላይ ያለውን fork ቁልፍን ጠቅ በማድረግ ይህንን ይጫኑት። ይህ በአንተ መለያ ውስጥ የዚህን repository ቅጂ ይፈጥራል።
አሁን Fork ይህን repository ወደ ማሽንዎ. ወደ GitHub መለያዎ ይሂዱ, የእርሶን repository ይክፈቱ. የኮድ ምልክቱን ጠቅ ያድርጉ እና ከዚያ ቅጂውን ምልክቱን ጠቅ ያድርጉ ለመቅዳት.
git clone "የቀዱትን url' ያስገቡ"
"የቀዱትን url' ያስገቡ" (ያለ ጥቅስ ምልክቶች) ይህ የዚህ repository url ነው(የእርሶ ቅጂ ፕሮጀክት). url ለማግኘት የቀደመውን ደረጃዎች ይመልከቱ.
ለምሳሌ:
git clone https://github.com/this-is-you/first-contributions.git
where this-is-you
የእርስዎ GitHub መለያ ስም ነው።. እዚህ በ GitHub ላይ ያለውን የመጀመሪያ አስተዋፅዖ repository ይዘቶችን ወደ ኮምፒውተርዎ እየገለበጡ ነው።
በኮምፒተርዎ ላይ ያለውን repository ማውጫ ይቀይሩ (እዚያ ከሌለዎት):
cd first-contributions
አሁን የ git checkout
ትዕዛዝን በመጠቀም ቅርንጫፍ ይፍጠሩ:
git checkout -b <add-your-new-branch-name>
ለምሳሌ:
git checkout -b github-ethiopia
አሁን የ Contributors.md ፋይልን በጽሑፍ አርታኢ(editor) ውስጥ ይክፈቱ፣ ስምዎን በእሱ ላይ ያክሉ። በፋይሉ መጀመሪያ ወይም መጨረሻ ላይ አይጨምሩት። በመካከል የትኛውም ቦታ ላይ ያስቀምጡት. አሁን, ፋይሉን ያስቀምጡ(save).
ወደ የፕሮጀክት ማውጫው ሄደው የ git status ከፈጸሙ ለውጦች እንዳሉ ያያሉ።
የ git add
ትእዛዝን በመጠቀም እነዚያን ለውጦች አሁን በፈጠሩት ቅርንጫፍ ላይ አክል፡
git add Contributors.md
አሁን የ git commit
ትዕዛዝ በመጠቀም እነዚህን ለውጦች ያድርጉ፡
git commit -m "Add <የእርስዎ-ስም> to Contributors list"
<የእርስዎ-ስም> ፋንታ የራስዎትን ስም ይጻፉ.
git push
የሚለውን ትዕዛዝ በመጠቀም ለውጦችዎን ይጫኑ
git push origin <የእርስዎ-branch-name>
<የእርስዎ-branch-name>
ፋንታ የራስዎትን branch ስም ያስገቡ
በ GitHub ላይ ወደ repository ከሄዱ፣ Compare & pull request
ጥያቄን ያያሉ። በዚያ ቁልፍ ላይ ጠቅ ያድርጉ።
አሁን pull request ጥያቄውን ያስገቡ
በቅርቡ ሁሉንም ለውጦችዎን ወደ የዚህ ፕሮጀክት ዋና ቅርንጫፍ አዋህዳለሁ. ለውጦቹ ከተዋሃዱ በኋላ የማሳወቂያ ኢሜይል ይደርስዎታል።
እንኳን ደስ ያለህ! አሁን መደበኛ fork -> clone -> edit -> pull request ሂደትን ጨርሰዋል. እንደ አስተዋጽዖ አበርካች ብዙ ጊዜ ይህ ሂደት ያጋትሞታል
አስተዋጾዎን ያክብሩ እና ለጓደኞችዎ እና ተከታዮችዎ ያካፍሉ ወደ ዲህረ ገጾ በመሄድ.
ማንኛውም እርዳታ ከፈለጉ ወይም ማንኛውም ጥያቄ ካለዎት የእኛን Slack ቡድን መቀላቀል ይችላሉ.
አሁን ለሌሎች ፕሮጀክቶች በማበርከት እንጀምር. እርስዎ ሊጀምሩባቸው የሚችሉ ቀላል ጉዳዮች ያላቸውን የፕሮጀክቶች ዝርዝር አዘጋጅተናል።. እኚህን ማስፈተሪያ ይከተሉ.
GitHub Desktop | Visual Studio 2017 | GitKraken |